
ለሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ የዲግሪ እና ቴክኒክና ሙያ ሴት ተማሪዎችን የኢንተርፕረነርሺፕ ሥልጠና ተሰጠ።
//////////////////////////////////////////////////
በኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) እና ሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ትብብር ዓለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንትን በማስመልከት ህዳር 02 እና 03 /2018 ዓ/ም ለኮሌጁ ተማሪዎች የኢንተርፕረነርሺፕ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
በኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) የአርባ ምንጭ ከተማ ፕሮጀክት አስተባባሪ ሙሉወርቅ በቀለ ተቋማቸው ከኮሌጁ ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ላለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ኮሌጁን ሀላፊዎች ጨምሮ ለአመራሮችና ለመምህራን ሥልጠናዎችን መስጠታቸውን ያስታወሱት አስተባባሪዋ የአሁኑም ሥልጠና ቀደም ሲል በተቋማቸው በሠለጠኑ መምህራን የተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኮሌጁ ፕረዚዳንት አቶ አለማየሁ ካሳ እንደገለጹት የተማሪዎችን የቢዝነስ አመለካከት በማሳደግ ከተቀጣሪነት አስተሳሰብ ማውጣት፣ የራስን ቢዝነስ መፍጠር የሚያስችል የአእምሮ ቀረጻና Mind set ወደ ቢዝነስ መግባት የሚያስችል ተነሣሽነት( creating a path for your Entrepreneurial success ,Business Opportunity Identification , starting a new business, Dream of running your own business?,መፍጠር ሥልጠናው ያተኮረባቸው ነጥቦችን ናቸው ፡፡
ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን በስፋት የሚፈልጉ የሥራ መስኮች መኖራቸውን እና የኢንተርፕረነርሺፕ ሥልጠናው ችግሮችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ከራስ አልፎ ለሌሎች የቢዝነስ መፍትሔ ለማምጣት የሚያግዝ በመሆኑ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት ለተማሪዎች አሰልጣኞች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በተጨማሪም ተማሪዎች ከሥራ ጠባቂነት ተላቀው የራሳቸውን ቢዝነስ መፍጠር እንዲችሉ እንዲሁም ተመርቀው ወደ ኢኮኖሚው ሲቀላቀሉ ሊገጥሟቸው የሚችሉ ፈተናዎችን በምን መልኩ ማለፍ እንደሚችሉ ግንዛቤ የሚሰጥ መሆኑን የተለያዩ በተማሪዎች አስተያየት በመስጠት እና ስልጠናውን ላጠናቀቁት ሴርተፍኬት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል ፡፡
ቀጣይ ተከታታይ ቀናት
Executive Entrepreneurship program
(Panel Discussion, Motivation speech, Events and seminar, Innovation business idea competition, Training program for teachers etc ) የሚቀጥል ይሆናል ።