26 April, 2024
0 Comments
1 category
ሳታ ተክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ የሠላም አነስተኛ ፋይናንስ የ100 ሺህ ብር አክሲዮን ግዥ ፈጽሟል።
የኮሌጁ ፕረዚዳንት አቶ አለማየሁ ካሳ በጋሞ ዞንና መላ ሃገሪቱ የስራ እድል ፈጠራ እና ለሃገር እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ሊያበረክት ምስረታ ላይ ለሚገኘው የሠላም አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከታቸው ደስታቸውን ገልጸዋል ።
ኮሌጁ በዞኑና በከተማው የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ፣እንዲሁም ለተቋማት የተለያዩ ሥልጠናዎችን እየሰጠ ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ የኮሌጁ ባለቤትና ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ካሳ ተናግረዋል።
ለሎች ተቋማት የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው እና ዞኑን አብረን በትብብርና በአንድነት እናልማ መልዕክታቸውን አሰተላልፈዋል ።
የሰላም አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አሰተባባሪዎች ሳታ ተክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
ቅድሚያ ለጋራ ልማት



Category: Uncategorized