
ሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ “በጋራ እንገንባ / Together We Build!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የኢንተርፕሪነርሽፕ ሳምንት አስመልክቶ የኢንተርፕረነርሺፕ ምክረ ሃሳብ መድረክ ( Entrepreneurship Dialogue) እና ስልጠና
በኮሌጁ ለሚገኙ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች ፤አሰልጣኞች እና ባለሙያዎች የኢንተርፕርነርሺፕ ስልጠና ተሰጠ ::
ስልጠናው የቢዝነስ እና የአመራር ኢንተርፕርነርሺፕ ጽንስ ሀሳብ Leading the Shift (21 the century Enterpunership skill, quality of leadership skill , Systems Thinking for Transformative Education) በሚል ርዕስ ለኮሌጁ ሰራተኞች፤አመራሮች እና አሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በኮሌጁ ፕረዝዳንት አቶ አለማየሁ ካሳ መስጠት ተችሏል::
ስልጠናው ትኩረት ያደረገባቸውን ነጥቦች ለመዘርዘር ያህል
- vision and Business Smart goal
2.Time Management with 24 hours,8/8/8 day to day routine activity )
3.Technolgy with AI ( business globalization)
4.Emotional intelligence (mind set , self- development, critical thinking, discipline)
5.Business mind set (Aspiration)
6.how to start business (big goal) - Business Challenges(idea , Capital,SWOT analysis)
8.Communication skill - Enterpunership with leadership concept
10.work-life balance (with business)
በስልጠናው ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ አካዳሚክ ጉዳዮች እና ጥናትና ምርምር ምክትል
ፕሬዘዳንት የሆኑት ፕሮፈሰር ተሾመ ይርጉ በንግግራቸው አዲሱ የዘርፉ እሳቤ ከዚህ በፊት ከለመድነው አካሄድ በተለየ አስተሳሰብ ተቋሙን ሊቀይሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ከፍ ብሎ ማሰብ ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን ሁላችንም የተሰጠንን ሀላፊነት በተገቢው መንገድ መወጣት ከቻልን እንደ ተቋም ለማሳካት ከያዝነው ግብ ለመድረስ ያስችለናልም ብለዋል::
የኮሌጁ መስራች እና ፕሬዘዳንት አቶ አለማየሁ ካሳ
በቀጣይ በአዲስ እይታ ኮሌጁን ወደፊት ሊያሻግሩ የሚችሉ ሀሳቦችን ይዘው የሚመጡ አካላትን ለመደገፍና እንደ ተቋም ኢንቨስት በማድረግ በጋራ ለመስራት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁነት መኖሩንም ገልፀዋል::
የዘርፉን ለውጥ የመምራት አስተሳብን የመላበስ የራስን ቢዝነስ በዘላቂነት የማመንጨት ሂደት ውስጥ የሚገጥሙ
ፈተናዎችን ጭምር የግል ተሞክሮዎችን ጋር በማመሳከር
ስልጠና ተሰጥቷል ።
በስልጠናው የጋሞ ዞን ቴክኒክና ሙያ ባለሙያዎች ቡድን ተሳታፊ ሲሆኑ ቀጣይም በተለያዩ ተጨማሪ ፕሮግራም ዕቅድ ተይዟል ።
ህዳር 10 ,2018 ዓ.ም አርባምንጭ ካምፓስ